Pages

Tuesday, August 2, 2011

ጣፋጭ ታሪክ

ጣፋጭ ታሪክ 
         ከብሥራት መጽሔት ቁጥር 28 አምስተኛ አመት 2003 ዓ.ም  የተወሰደ 
         ዮሴፍ አረጋ

‹‹ ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም››
በአንድ ጥቅጥቅ ባለ ደን ውስጥ እንጨት ሰብራ ጎጆዋን ሰርታ የተለያዪ ነገሮችን ፈላልጋ ጫጩቶቿን የምትመግብ እና በደን ውስጥ ከሚገኙት ትላልቅ ዛፎች መካከል በቁመቱ ገዘፍ ካለው ዛፍ ላይ ኑሮዋን የመሰረተች አንዲት አሞራ ነበረች….. በዚህም ቁመታም ዛፍ ግርጌ ደግሞ ውፍረቷ ያስቸገራት ነገር ግን ከዚያም ከዚህም ብላ ቅጠላ ቅጠል ፈላልጋ ልጆቿን የምትንከባከብ ደግነቷ በሀገር የተመሰከረላት አሳማ ነበረች፡፡ ይሁን እንጂ በዚ ቁመቷ ዛፍ ላይ ደግሞ እርጉዟ ውሮ መኖር ከጀመረች ሰንበትበት ብላለች፡፡
ታዲያ ወ/ሮ ድመት እርግዝናዋ እየገፋ መውለጃዋ እየደረሰ መምጣቱ የምትወልደውን ሙጪሊቶች ከላይ ያለችው ጎረቤት አሞራ ከታች ያለችው  ጎረቤት አሳማ ነጥቀውና ረግጠው እንዳይበሉባትና እንዳይረግጡባት ሰጋች፡ ዝም ካለች አሞራ አንድ ቀን በጥፍሯ ልጆቿን ቆንጥጣ አንስታ እንዳትወስድባት ድንገት ደግሞ ወደታች ወድቀው አሳማ በውፍረቷ ረግጣ እንዳትገድልባት ስትል መላ ዘየደች፡፡
በንጋታው ወ/ሮ ውሮ የዚያን ትልቅ ዛፍ ቅርንጫፍ ለቅርንጫፍ እየዘለለች ወደ ላይ ካለችው አሞራ ዘንድ ሄደች ወደ ቤም ጠጋ ብላ ‹‹ወዳጄ አሞሪት እንደምን ሰንብተሻል? ›› አለች ፡ አሞራም ‹‹እንዴት ከርመሻል እቴ ድመት ቆንጆ›› ብላ መለሰችላት ድመትም አፏን አሹላ ‹‹የአዲስ ጫጩቶችሽን ድምጾች እቤት ሁኜ እየሰማሁ ልቤ እያዘነ ዓይኔ ማንባት ጀምሯል›› ብላ ጎንበስ አለች፡፡ አሞራም በክንፎ ድመቷን ነካ እያደረገች ለምን እንደምታዝን እንድተነግራት ወተወተቻት፡፡ ወ/ሮ ውሮም ቀጥሎ የምትነገራትን ለማንም እንዳትናገር አስጠንቅቃት ‹‹ታች መሬት ላይ የምትኖረው አሳማ እኔ እና አንቺ ከዚህ ብር ብለን እንድንጠፋ የዛፉን ዳር ዳር እየቆረቆረች ዛፉ እስኪገነደስ ድረስ እንደምትቀጥል ለጓደኞ ስትናገር ሰማሁ›› ብላ ተናገረች አሞራም መልሳ ‹‹የተከበርሽ ውሮ ሆይ አትጨነቂ እኔ እንደሆነ ከዚች የደሃ ጎጆዬ ንቅንቅ አልልም›› ብላ በመለሰችላት ጊዜ ውሮም የአሞሪትን መስተንግዶ አመስግና ቅርንጫፍ ለ ቅርንጫፍ እየዘለለች ወደ ቤቷ ሄደች፡፡
አመሻሽ በሆነ ጊዜ ውሮ ከመኖሪያዋ ወደ አሳሚት መኖሪያ ወረደችና ለአሳማ የከበረ ሰላምታዋን አቅርባ አረፍ እንዳለች ዓይኗን ፍዝዝ አድርጋ ፀጥ አለች፡፡ አሳማዋም በአዲሱ የድመት ባህሪ ተገርማ ምን እንደነካት ጠየቀቻት፡፡ ውሮም ‹‹እኔ በምወልዳቸው ሙጪሊቶቼና በአንቺ ልጆች መካከል የታሰበ ሤራ አለ›› ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፡፡ አሳማዋም ጉዳዩን ለማንም እንደማታወራ ውሮ ከማለችላት ብቻ እንደምትነግራት በዝግታ ተናገረች፡ አሳማዋም ለማንም እንደማትናገር ቃል ገባች፡፡
ውሮም  …. ‹ሚያው› ብላ ጉሮሮዋን ጠራርጋ ‹‹ከዚች ከእኛ በላይ ያለችው ጎረቤታችን አሞራ አንቺ ጠዋት ለስራ ስትወጪ እኔ ደግሞ ሙጪሊቴን ስወልድ ጠብቃ በነዚያ በሚያስጠሉ ጥፍሮቿ ልጆቻችንን ከጉያችን ልትመነትፍ ተዘጋጅታለች›› አለች ቁና ተንፍሳ እና ምን ይሻላል ብላ በእጆቿ ፊቷን ጠራረገች….›› አሳማዋም ‹‹ወዳጄ ውሮ ከዚህ በíላ ከዚች ቦታዬ ንቅንቅ አልልምና አታስቢ ስለ ምክርሽ አመሰግናለው›› አለች፡፡
ከዚያች ቀን ጀምሮ አሳማዋም አሞራዋም ዛፋቸውን ሳይለቁ በቦታቸው አድፍጠው ስለ ልጆቻቸው እያሰቡና እየቆዘሙ ወ/ሮ ድመት የነገረቻቸውን ጉዳይ አምነው ውለው አደሩ፡ ምግብ ጠፋ፡ በነዚህ ሁለት ጎረቤቶች መካከል የሚፈጠረውን ለማየት ውሮም በቦታዋ አድፍጣ ቆየች፡፡
ቀናት አለፉ መሸም… ነጋም… የአሞራይቱና የአሳማዋ ልጆች በረሃብ አንጀታቸው ታጥፎ ሞቱ… የሞት ነገር ግን በዚህ አላበቃም አንዱ አንዱን አድፍጦ ሲጠብቅ ድመትም መጨረሻውን ለማየት ስትል ከቦታቸው ሳይነቃነቁ ሰነበቱ ረሀቡን ግን የቻለ ማንም የለም፡፡ ሁሉም በያለበት ፍንግል ፍንግል እያለ የሞትን ፅዋ ተጎነጩ፡ ሌሎችን አጣልታ ለመኖር ያቀደችው ውሮም በረሃቡ ምክንያት ህይወቷን ገበረች፡፡
ጌታ ሆይ የፍቅርን መንፈስ በላያችን አሳድር፡፡  

No comments:

Post a Comment