ዋጋው የላቀ ልዩ ስጦታ
(ይህ ታሪክ እ.ኤ.አ. በ 2003 በሎስ አንጀለስ ታይምስ ላይ ቀርቦ የነበረ ነው)
እንዲህ ሆነ …
ወጣቱ ቢል የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ሊያጠናቅቅ ጥቂት ወራት በቻ ቀረተውታል፡፡ በሀገሬው ልማድ መሰረትም ወላጅ አባቱ ትምህርቱን ላጠናቀቀው ልጁ መኪና ገዝቶ መሸለም ግድ ይለው ነበር፡፡
ለተከታታይ ቀናትም ቢል የሚገዛለትን መኪና በማሰብ፤ በማየትና፡ የሚስማማውን ሞዴል በመምረጥ ሰነበተ፡፡… ጊዜውም ደረሰ ትምህርቱ በሰላም ተጠናቀቀ ት/ቤቱም አስመረቀው፡፡ ከምርቃት መርሃ ግብር በíላ ቢል ወዲህና ወዲያ ሳይል ወደ ቤተሰቦቹ ዘንድ ገሰገሰ .. በሀሳቡም ያቺን ቀልቡ ያረፈበትን መኪና መግዣ ቼክ ከኣባቱ እጅ ሲቀበል ታየው፡፡
የቢል አባት ልጃቸው ወደ ቤቱ መምጣቱን ባዩ ጊዜ በመመረቁ ደስታቸውን አቅፎ በመሳም ከገለጹለት በíላ በልዩና ባማረ የስጦታ መጠቅለያ የተጠቀለለሰ መጠኑ ገዘፍ ያለ ነነር ለልጃቸው ሰጡት … ቢል በጥድፊያ ያንን መጠቅለያ ከፈተው ባየውም ነገር ተገረመ .. ስጦታው መጽሐፍ ቅዱስ ነበር… ቢል የሚየዘው የሚጨብጠው ጠፋው እጅግ ተናደደ እርሱ ያሰበው የገንዘብ ቼክ የተሰጠው ግን መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑ ይበልጥ አስከፋው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱን ወደ አንድ ጥግ ወርውሮ የቤቱን መዝጊያ ሳይዘጋ ወደ ደጅ ወጣ ቤተሰቦቹም ተከተሉት ነገር ግን ሊደርሱበት አልቻሉም፡፡
ቢል ከቤት እንደወጣ አልተመለስም በዚያው የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ ቀናት …
ሳምንታት … ወራት አለፉ በአጋጣሚ ወላጅ አባቱም ሕይታቸውም በድንገት ያልፋል የአባቱን ሞት የሰማው ቢል በቀብር ስነ ሥረኣታቸው ላይ ተገኘ፡፡ ከቀብር መልስ ወደ ቤታቸውም ተመለሱ ቢል ማሰላሰልና ማብሰልሰል ቀጠለ፡፡
ጊዘው መሸትሸት እንዳለ ያኔ አባቱ በምርቃቱ ሥነ-ሥርኣቱ ላይ የሰጡትን መጽሓፍ ቅዱስ ከተቀመጠበት ቦታ በርብሮ አወጣው፡፡ በእጁም እንደጨበጠው ለተወሰነ ደቂቃ በዝምታ ተዋጠ መጽሓፍ ቅዱሱንም እንደከፈተው ያቺን የመረጣትን የመኪና መግዣ መጠን ያህል ገንዘብ የያዘ ቼክ በውስጡ አገኘ … የሚገርመው ነገር ደግሞ ቼኩ የተፈረመበት ዕለትና ጊዜ… ከምርቃቱ ቀኑ ጋር አንድ ነበር… አባቱ የእግዚአብሔርን ቃል ከቼኩ ጋር አብረው ለመስጠት ፈልገው ኖሯል፡፡ ቼኩን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተው የሰጡት ….ይህንን ባየ ጊዜ ምርር ብሎ አለቀሰ ስሀተቱንም ተረዳ ….አባቱ ግን ዳግመኛ ላይመለሱ ሄደዋል፡፡
ምናልባት ይህ ሰነፍ ልጅ አንድ ቀን መጽሐፍ ቅዱስን ከፍቶ ማንበብ ሲጀምር ‹‹ሰነፍ ልጅ ለአባቱ ፀፀት ነው፤ ለወለደችውም ምሬት ነው›› ምሳ 17፡25 የሚለውን ቃል ያነብ ይሆን?
ከብሥራት መጽሔት ቁጥር 24 አራተኛ አመት 2003 ዓ.ም የተወሰደ
ዮሴፍ አረጋ
ዮሴፍ አረጋ
No comments:
Post a Comment