Pages

Monday, September 19, 2011

የጽናት ዋጋ ስንት ነው?

የጽናት ዋጋ ስንት ነው?
በሚካኤል ተሾመ
ጥያቄ ልጠይቅ?! ክርስቲያን ኖት … ካልተሳሳትኩ! ጥያቄዬ ግልጽ የሚሆንሎት ክርስቲያን ከሆኑ ብቻ ነው ብዬ ነወ፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወትዎ ዓላማዎ ምንድነው? ካነበቧቸው መጻሕፍት ዓላማ ኖሮት የተሳካለት ሰው ያውቃሉ? አሁን የነገሩኝ ሰው የሕይወት መመሪያዎቹ ምን ምን ናቸው? ዓላማውስ ለመከተል ያደረገው ምንድነው?
ደስታ፤ ሰላም ፤ ሕልም እውን የመሆን፤ የመከራን ክበር፤ ወይስ ምን?.... እስቲ አንዴ በህሊናዎ የርሱን ሕይወት ይቃኙት … ለዚህ ክብር ለመብቃት የተከፈለው መስዋትነት ምን ነበር? እስር ቤት ፤ እንግልት፤ በሰዎች መናቅ፤ ረኃብ… ምን? እነዚህ ሰውን ከዓላማው የሚየስቱ፤ እውነት ብለን ከያዝነው የሚስያክዱ ነገሮች ናቸው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹በፈተና የመጸና የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በíላ ለሚወለዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወት አክሊል ይቀበላልና›› ይላል፡፡ መከራ ክብር አለው፡፡ ከእያንዳንዱ መከራ ጀርባ ሽልማት አለ፡፡ ችግሩ ግን በእነዚህ መከራዎች መካከል ራስን ደስተኛ ሆኖ ማሰብ ‹‹ላም አለኝ በሰማይ…›› ሊያሰኝ ይችላል፡፡ ‹‹የማያልፍ የለም …የደስታ ቀን ያልፋል፤ የመከራ ቀንም ያልፋል…›› ብሎ ትዕግስትን ገንዘብ ማድረግ ‹‹ሞኝ በእባብ ሁለቴ ይነደፋል አንዴ ሲያይ›› ሊባል ይችላል፡፡
ዋናው ጥያቄ በመከራ ውስጥ ማን ይጸናል ነው፡፡ ማንስ በፈተና ውስጥ ቀና ብሎ የነገን ሊያይ፤ መልካሙን ሊያስብ፤ ጠላቶቹን ይቅር ሊል ይችላል? መከራ ሲበዛ ይመራል፡፡ በሮች ሁሉ፤ መስኮቶች ሁሉ ዝግ፤ መንገዶች ሁሉ ጠባብ፤ ፍሬዎች ሁሉ መራራ፤ ቀኑ ሁሉ ሌሊት ፤ ምሽቱ ሁሉ የማይነጋ እንደሆነ ሊሰማን ይችላል፡፡ ይሄን ጊዜ የቅርብ ወዳጃችን እንባችን ይኾናል፡፡
ለዓላማችን ያለን ጽናት በመከራ ይፈተናል፡፡ እምነታችን በሚገጥመን መከራ ይለካል፡፡ ስንዴ ካልሞተች በስብሳ ፍሬ አታፈራም፤ ሰውም በመከራ ካልታሸ ፍሬ አያፈራም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሕይወት ተሞክሯቸው ስለዓላማ ጽናት የሚየሰተመሩንን እናገኛለን ወይም አንብበናል፡፡
ኖኅ አብርሃም፤ ሎጥ ሙሴ፤ ኢያሱ፤ ዳነኤል፤ ኤርሚያስ፤ አሳይያስ፤ ዮሴፍ፤ ቅ/ጳውሎስ… ይቀጥላል፡፡ አንድን ሰው ጽናቱን ለመመዘን፤ ዓላማውን ለማሳት የሚቀርቡት ቅድመ ሁኔታዎች መከራ፤ ጭንቀት፤ ስደት፤ ረኃብ፤ ራቁትነት፤ ፍርሃት ወይም ሰይፍ ሁሉ አላስፈራቸውም፡፡ ያላቸውን ሁሉ ጥለው፤ ትዕግስትን ቤት፤ ተስፋን ግድግዳ፤ እምነትን መሰረት፤ ሰላምን ጣሪያ፤ ፍቅርን ምሰሶ፤ ጽናትና ማገር አድርገው ዓላማቸውን እየተከተሉ ፍኖታቸውን ትተውልን ሄዱ፡፡ ስለዘህም ‹‹ስጋን ከክፉ መሻቱ እና ከምኞቱ ጋራ ሰቀሉ፡፡››
ሙሴ ብድራቱን ትኩር ብሎ ስለተመለከተ የፈርዖን የልጅ ልጅ መባልን በእምነት እምቢ አለ፤ በዓላማው ጸና፤ አብርሃም የዘመዶቹን ስድብ ሳያስብ እግዚአብሔርን ለመፈለግ የሚሄድበትን ሳያውቅ በእምነት ከቤቱ ወጣ፤ በዓላማው ጸና፡፡
ኖኅ በአሕዛብ መካከል ተቀምጦ  ለእግዚኣብሔር ለመገዛት ስለወሰነ የኀጢያተኞችን ስድብ ሳያፍር መርከብን በእምነት አዘጋጀ፤ በኣለማው ጸና፤ ኢያሱ በበረሓው መካካል ‹‹እኔና ቤቴ እግዚኣብሔርን እናመልካለን እናንተ ግን የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ›› አለ ፤ በኣላማው ጸና ፤ ዮሴፍ እግዚኣብሔርን በታማኝነት ማገልገል ከሁሉ የሚሻል መሆኑን ስላወቀ በእስር ቤት ተጥሎ እስከሚረሳ ድረስ አምላኩን አሰበ፤ በዓላማው ጸና፡፡
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገጥመን መከራ ሳንደናገጥ ለኣላማችን ተገዥ ብቻ እንድሆን ‹‹ልባችሁ አይታወክ አይፍራም፤ በእኔም እመኑ ፤ በኣባቴም እመኑ›› በማለት መክሮናል፡፡ በዓላማ መጽናት ምንድነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------  
ሚካኣል ተሾመ ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ በህግ ትምህርት የመጀመሪያውን ዲግሪ  የያዘ ሲሆን በቀድሞዋ አዲስ ነገር ጋዜጣና በሌሎችም የህትመት ውጤቶች የተለያዩ ፅሁፎችን በመጻፍ ይታወቃል፡፡ 

Monday, August 22, 2011

እርሱ እጅግ የሚፈራዊ የራሱን ጥላ ሲያይ ነው

“…. እርሱ እጅግ የሚፈራዊ የራሱን ጥላ ሲያይ ነው….”
በነበረበት ጊዜና ከዚያም በíላ ከተነሱት ነገስታት ሁሉ በጥበቡና በታላቅነቱ ይታወቅ ነበር፤ ታላቁ እስክንድር ገና በሥጋ ዘመኑ አባቱን በመከተል በምክትል ማዕረግ የተወለደበትን ሀገር ይመራ ነበር፡፡ ዕድሜው ወደ አስራስምንት አካባቢ ሲደርስ ታላቅ የጦር መሪ ሊሆን ቻለ፡፡ የመቄዶንያንና ሌሎች ግዛቶችን ደግሞ በ20ኛው ዕድሜ መጀመሪያ አካባቢ በንጉስነት አገለገለ፡፡
እንዲ ሆነ…… አንድ ፊሊኒክስ የተባለ ተሰሎንቄያዊ የነገስታቱን የፈረስ ጋጣ ይጠብቅና ይመራ ዘንድ ኃላፊነት የተሰጠው ሰው ነበር፡፡ ታዲያ በአንድ ወቅት ወደ ታላቁ እስክንድር አባት ጠጋ ብሎ ከጋጣው ውስጥ ያለ አንድ ፈረስ ለመግራትና ለመጋለብ እምቢ እንዳለ በጣምም ስላስቸገረ ሊሸጥ እንደሚገባ ይመክረው ጀመር፡፡
ይህን መክክር የሰማው ታላቁ እስክንድር በወጣትነት ኃይሉ በመገፋፋት ‹‹ከፊሊኒክስ ጋር ፈረሶቹ ጋጣ ሄጄ ይህንን አውሬ የሆነ ፈረስ ማየት አለብኝ›› ብሎ አባቱን ወተወተ፡፡ አባቱም ስለ ልጁ በመሳሳት እንዳይሄድ ከለከለው፤ ታላቁ እስክንድር ግን ‹‹ አባቴ ሆይ ምንም አልሆንም አትፍራ፤ ይሄ ፈረስ አልገራ ያለበት አንድ ምክንያት ቢኖር ነውና እስቲ እኔ ሄጄ ለመግራት ልሞክረው እባክህን ፍቀድልኝ?›› ብሎ በድጋሚ አባቱን ለመነ ንጉሱም  ‹‹ከፊሊኒክስ የበለጠ የመግራት ልምድ ያለህ አይመስለኝም ፊሊኒክስ እድሜውን በሙሉ እንስሳትን በመግራትና በማለማመድ እንደቆየ ልብ በል›› አለው፤ እስክንድርም መልሶ ‹‹ አባቴ ሆይ ልክ ብለሃል ፈረሶቹን የመግራት ልምድ የለኝም ፡ ግን የዚህን አውሬ የሆነ ፈረስ ፀባይ እና እምቢ ባይነቱን ማወቅ አለብኝ፡፡›› ብሎ መለሰለት፡፡
ወጣቱ እስክንድርም ወደ ታላቁ ቤተመንግስት ፈረስ ጋጣ ከፊሊኒክስ ጋር አመራ ፊሊኒክስም ወደ አስቸጋሪው ፈረስ ጠጋ ብሎ ለመያዝና ለመግራት ሲሞክር በጋጣው ውስጥ የነበረ ግርግርና የፈረሱ ማስቸገር እጅግ በዛ፡፡ በዚህ ጊዜ ወጣቱ እስክንድር በፍጥነት የፈረሱን ልጓም በመያዝ ከነበረበት አቅጣጫ አዞረው፤ ወዲያውኑ አስቸጋሪው ፈረስም ተረጋጋ ለዘብም አለ፡፡ እስክንድርም በተረጋጋ መንፈስ ፈረሱን አሰለጠነው፤ ጋለበውም ፈረሱንም እየጋለበ ወደ አባቱ ዘንድ ወሰደው፡ አባቱም በልጁ ጥበብ በመደነቅ በዚች ትንሽ ጊዜ ውስጥ አስቸጋሪውን ፈረስ በመግራቱ በመገረም ‹‹ልጄ እስክንድር ሆይ ምን ጥበብ ብትጠቀም ነው እንዲ የተገራልህ?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ እስክንድርም ‹‹አባቴ ሆይ ነገሩ ቀላል ነው፡ ፈረሱ ሁልጊዜ ከፊት ለፊት የራሱን ጥላ ሲያይ እጅግ ይፈራል፤ በዚህ ጊዜም ያስቸግራል፤ ስለዚህ የፈረሱን ልጓም ይዤ ፊቱን ወደ ፀሀይ አቅጣጫ አዞርኩት፤ ይሄኔም የራሱ ጥላ በእግሮቹ ኮቴ ስር ሲሆን መፍራቱንም ማስቸገሩንም ተወ ተረጋጋ›› ብሎ መለሰለት፡፡
እውነት ነው…….በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ህዝቦች የራሳቸውን ጥላ ሲያዩ ይፈራሉ፡፡ ነገር ግን አይናቸውን ወደ ፀሀይ ፅድቅ ቢያዞሩ ጥላ የሚባለውን ፍራቻ ከቶ አያዩም፤ጥላቸውም በእግራቸው ኮቴ ስር ይወድቃል፤ ፍርሀቱም በእምነትና በእግዚአብሔር ጥባቆት ይተካል፡፡
ወደ ክርስቶስ እንቅረብ … እርሱ ፀሀየ ፅድቅ ነውና ጥላችንን በእግራችን ስር ይጥለዋል፡፡ የጌታን ድምጽ በተለይም ‹‹ብርሃን ከእናንተ ጋር ነው….. ብርሃን ሰላላችሁ ተመላለሱ …..የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃን ስላላችሁ በብርሃን እመኑ›› ዮሐ 12፡35-36 /የሚለውን ትሰማላችሁ፡፡
የፅድቅ ፀሐይ ሆይ ለነፍሴ ብርሀንን ስጣት፤ ብርሃንህንም ባየች ጊዜ ጥላዋ በእግሮችዋ ኮቴ ስር ይወድቃሉ ያን ጊዜም ….የራሴን ጥላ መፍራት አልጀምርም፡፡  
            ምንጭ ፡ spring of love 

ከብሥራት መጽሔት ቁጥር 23 አራተኛ አመት 2001 ዓ.ም  የተወሰደ ዮሴፍ አረጋ   

Thursday, August 11, 2011

ዋጋው የላቀ ልዩ ስጦታ

ዋጋው የላቀ ልዩ ስጦታ
(ይህ ታሪክ እ.ኤ.አ. በ 2003 በሎስ አንጀለስ ታይምስ ላይ ቀርቦ የነበረ ነው)
እንዲህ ሆነ …
ወጣቱ ቢል የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ሊያጠናቅቅ ጥቂት ወራት በቻ ቀረተውታል፡፡ በሀገሬው ልማድ መሰረትም ወላጅ አባቱ ትምህርቱን ላጠናቀቀው ልጁ መኪና ገዝቶ መሸለም ግድ ይለው ነበር፡፡
ለተከታታይ ቀናትም ቢል የሚገዛለትን መኪና በማሰብ፤ በማየትና፡ የሚስማማውን ሞዴል በመምረጥ ሰነበተ፡፡… ጊዜውም ደረሰ ትምህርቱ በሰላም ተጠናቀቀ ት/ቤቱም አስመረቀው፡፡ ከምርቃት መርሃ ግብር በíላ ቢል ወዲህና ወዲያ ሳይል ወደ ቤተሰቦቹ ዘንድ ገሰገሰ .. በሀሳቡም ያቺን ቀልቡ ያረፈበትን መኪና መግዣ ቼክ ከኣባቱ እጅ ሲቀበል ታየው፡፡
የቢል አባት ልጃቸው ወደ ቤቱ መምጣቱን ባዩ ጊዜ በመመረቁ ደስታቸውን አቅፎ በመሳም ከገለጹለት በíላ በልዩና ባማረ የስጦታ መጠቅለያ የተጠቀለለሰ መጠኑ ገዘፍ ያለ ነነር ለልጃቸው ሰጡት  … ቢል በጥድፊያ ያንን መጠቅለያ ከፈተው ባየውም ነገር ተገረመ .. ስጦታው መጽሐፍ ቅዱስ ነበር… ቢል የሚየዘው የሚጨብጠው ጠፋው እጅግ ተናደደ እርሱ ያሰበው የገንዘብ ቼክ የተሰጠው ግን መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑ ይበልጥ አስከፋው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱን ወደ አንድ ጥግ ወርውሮ የቤቱን መዝጊያ ሳይዘጋ ወደ ደጅ ወጣ ቤተሰቦቹም ተከተሉት ነገር ግን ሊደርሱበት አልቻሉም፡፡
ቢል ከቤት እንደወጣ አልተመለስም በዚያው የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ ቀናት …
ሳምንታት … ወራት አለፉ በአጋጣሚ ወላጅ አባቱም ሕይታቸውም በድንገት ያልፋል የአባቱን ሞት የሰማው ቢል በቀብር ስነ ሥረኣታቸው ላይ ተገኘ፡፡ ከቀብር መልስ ወደ ቤታቸውም ተመለሱ ቢል ማሰላሰልና ማብሰልሰል ቀጠለ፡፡
ጊዘው መሸትሸት እንዳለ ያኔ አባቱ በምርቃቱ ሥነ-ሥርኣቱ ላይ የሰጡትን መጽሓፍ ቅዱስ ከተቀመጠበት ቦታ በርብሮ አወጣው፡፡ በእጁም እንደጨበጠው ለተወሰነ ደቂቃ በዝምታ ተዋጠ መጽሓፍ ቅዱሱንም እንደከፈተው ያቺን የመረጣትን የመኪና መግዣ መጠን ያህል ገንዘብ የያዘ ቼክ በውስጡ አገኘ … የሚገርመው ነገር ደግሞ ቼኩ የተፈረመበት ዕለትና ጊዜ… ከምርቃቱ ቀኑ ጋር አንድ ነበር… አባቱ የእግዚአብሔርን ቃል ከቼኩ ጋር አብረው ለመስጠት ፈልገው ኖሯል፡፡ ቼኩን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተው የሰጡት  ….ይህንን ባየ ጊዜ ምርር ብሎ አለቀሰ ስሀተቱንም ተረዳ ….አባቱ ግን ዳግመኛ ላይመለሱ ሄደዋል፡፡
ምናልባት ይህ ሰነፍ ልጅ አንድ ቀን መጽሐፍ ቅዱስን ከፍቶ ማንበብ ሲጀምር  ‹‹ሰነፍ ልጅ ለአባቱ ፀፀት ነው፤ ለወለደችውም ምሬት ነው››   ምሳ 17፡25 የሚለውን ቃል ያነብ ይሆን?

ከብሥራት መጽሔት ቁጥር 24 አራተኛ አመት 2003 ዓ.ም  የተወሰደ 
         ዮሴፍ አረጋ        

Wednesday, August 3, 2011

WHY PRETENDING?


WHY PRETENDING?
Ayalew Mekonnen
             You might have come across a person who has become famous by publicizing somebody else's creative work as his own. It is not also uncommon to see an individual running to get thanks at the disadvantage of the right person in different spheres of life.
             To me pretentious talk and pretentious use of phones and cars is nothing short of claiming somebody's result of hard work. I say this because I have closely seen what has happened to a certain driver in my former organization. The organization has got more than fifteen code 03 cars. Using one of these cars the driver is accustomed to behaving like owner of the car he drives. Manager of the Organization has been informed about the driver's conduct. On the last Monday evening he was late to give service because of spending time with his girlfriend who considers him as owner of the car. The Manager with two police men has been following him. And they saw him beating up his girlfriend sitting in the car. The Manager appeared and immediately asked why he was beating her. Before he responds she started to argue for him in spite of his mistakes. Unfortunately the Manager seized the key from the car. "Previously the driver was advised many times not to do so”, the manager said. So on the spot the driver has lost both his job and his beautiful lady. Why pretending?
      In connection with this let me share with you about a certain employee. The guy was newly hired person. He is a kind of person whose words speak louder than his actions. Two days after he received letter of employment he entered office and picked up phone in the office and started speaking to naught. He called nobody but he wanted to show how busy and committed he is. While he was talking over the phone to nobody a telephone technician appeared and even entered that office. He sat to wait for him till he finishes calling. The newly hired employee finished his talk and asked the technician what he could help him. The technician said "I came to your office to install the phone". Shame on the employee!
      You might also have seen somebody who carries big cell phone that doesn't work but who holds closer to his ear acting as if he is calling. I have met a person who is also on hot chatting over mobile phone by the time there wasn't network coverage in the city.
      In related move some people may try somehow to grab attention by using few words of certain language they don't know well. Instead of admitting their inability they tend to mix up or misuse words and confuse others. Knowing ten words of French language couldn't make me fluent speaker of the language. Better to admit than pretending. A renowned author of You Can Win, Shiv Khera says a person who thinks knows a lot has also a lot to learn!

Ato Ayalew Mekonnen is nowadays one of the influential journalists in Ethiopian Media. He got his BA in Non-teaching history and English & Journalism Minor from Addis Ababa University. Previously, he worked for Radio Fana Broadcasting Corporate as Reporter and Deputy Producer. Ato Ayalew has worked also for Oromia TV as Chief Editor and Newscaster of English news. He has superb writing and editing skills on TV and Radio programs and news. And recently with Wafa Marketing and Promotion   Company Ayalew has successfully carried out various communications activities.
Ayalew can be reached at: ayalewmekonnen@yahoo.com

Tuesday, August 2, 2011

ጣፋጭ ታሪክ

ጣፋጭ ታሪክ 
         ከብሥራት መጽሔት ቁጥር 28 አምስተኛ አመት 2003 ዓ.ም  የተወሰደ 
         ዮሴፍ አረጋ

‹‹ ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም››
በአንድ ጥቅጥቅ ባለ ደን ውስጥ እንጨት ሰብራ ጎጆዋን ሰርታ የተለያዪ ነገሮችን ፈላልጋ ጫጩቶቿን የምትመግብ እና በደን ውስጥ ከሚገኙት ትላልቅ ዛፎች መካከል በቁመቱ ገዘፍ ካለው ዛፍ ላይ ኑሮዋን የመሰረተች አንዲት አሞራ ነበረች….. በዚህም ቁመታም ዛፍ ግርጌ ደግሞ ውፍረቷ ያስቸገራት ነገር ግን ከዚያም ከዚህም ብላ ቅጠላ ቅጠል ፈላልጋ ልጆቿን የምትንከባከብ ደግነቷ በሀገር የተመሰከረላት አሳማ ነበረች፡፡ ይሁን እንጂ በዚ ቁመቷ ዛፍ ላይ ደግሞ እርጉዟ ውሮ መኖር ከጀመረች ሰንበትበት ብላለች፡፡
ታዲያ ወ/ሮ ድመት እርግዝናዋ እየገፋ መውለጃዋ እየደረሰ መምጣቱ የምትወልደውን ሙጪሊቶች ከላይ ያለችው ጎረቤት አሞራ ከታች ያለችው  ጎረቤት አሳማ ነጥቀውና ረግጠው እንዳይበሉባትና እንዳይረግጡባት ሰጋች፡ ዝም ካለች አሞራ አንድ ቀን በጥፍሯ ልጆቿን ቆንጥጣ አንስታ እንዳትወስድባት ድንገት ደግሞ ወደታች ወድቀው አሳማ በውፍረቷ ረግጣ እንዳትገድልባት ስትል መላ ዘየደች፡፡
በንጋታው ወ/ሮ ውሮ የዚያን ትልቅ ዛፍ ቅርንጫፍ ለቅርንጫፍ እየዘለለች ወደ ላይ ካለችው አሞራ ዘንድ ሄደች ወደ ቤም ጠጋ ብላ ‹‹ወዳጄ አሞሪት እንደምን ሰንብተሻል? ›› አለች ፡ አሞራም ‹‹እንዴት ከርመሻል እቴ ድመት ቆንጆ›› ብላ መለሰችላት ድመትም አፏን አሹላ ‹‹የአዲስ ጫጩቶችሽን ድምጾች እቤት ሁኜ እየሰማሁ ልቤ እያዘነ ዓይኔ ማንባት ጀምሯል›› ብላ ጎንበስ አለች፡፡ አሞራም በክንፎ ድመቷን ነካ እያደረገች ለምን እንደምታዝን እንድተነግራት ወተወተቻት፡፡ ወ/ሮ ውሮም ቀጥሎ የምትነገራትን ለማንም እንዳትናገር አስጠንቅቃት ‹‹ታች መሬት ላይ የምትኖረው አሳማ እኔ እና አንቺ ከዚህ ብር ብለን እንድንጠፋ የዛፉን ዳር ዳር እየቆረቆረች ዛፉ እስኪገነደስ ድረስ እንደምትቀጥል ለጓደኞ ስትናገር ሰማሁ›› ብላ ተናገረች አሞራም መልሳ ‹‹የተከበርሽ ውሮ ሆይ አትጨነቂ እኔ እንደሆነ ከዚች የደሃ ጎጆዬ ንቅንቅ አልልም›› ብላ በመለሰችላት ጊዜ ውሮም የአሞሪትን መስተንግዶ አመስግና ቅርንጫፍ ለ ቅርንጫፍ እየዘለለች ወደ ቤቷ ሄደች፡፡
አመሻሽ በሆነ ጊዜ ውሮ ከመኖሪያዋ ወደ አሳሚት መኖሪያ ወረደችና ለአሳማ የከበረ ሰላምታዋን አቅርባ አረፍ እንዳለች ዓይኗን ፍዝዝ አድርጋ ፀጥ አለች፡፡ አሳማዋም በአዲሱ የድመት ባህሪ ተገርማ ምን እንደነካት ጠየቀቻት፡፡ ውሮም ‹‹እኔ በምወልዳቸው ሙጪሊቶቼና በአንቺ ልጆች መካከል የታሰበ ሤራ አለ›› ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፡፡ አሳማዋም ጉዳዩን ለማንም እንደማታወራ ውሮ ከማለችላት ብቻ እንደምትነግራት በዝግታ ተናገረች፡ አሳማዋም ለማንም እንደማትናገር ቃል ገባች፡፡
ውሮም  …. ‹ሚያው› ብላ ጉሮሮዋን ጠራርጋ ‹‹ከዚች ከእኛ በላይ ያለችው ጎረቤታችን አሞራ አንቺ ጠዋት ለስራ ስትወጪ እኔ ደግሞ ሙጪሊቴን ስወልድ ጠብቃ በነዚያ በሚያስጠሉ ጥፍሮቿ ልጆቻችንን ከጉያችን ልትመነትፍ ተዘጋጅታለች›› አለች ቁና ተንፍሳ እና ምን ይሻላል ብላ በእጆቿ ፊቷን ጠራረገች….›› አሳማዋም ‹‹ወዳጄ ውሮ ከዚህ በíላ ከዚች ቦታዬ ንቅንቅ አልልምና አታስቢ ስለ ምክርሽ አመሰግናለው›› አለች፡፡
ከዚያች ቀን ጀምሮ አሳማዋም አሞራዋም ዛፋቸውን ሳይለቁ በቦታቸው አድፍጠው ስለ ልጆቻቸው እያሰቡና እየቆዘሙ ወ/ሮ ድመት የነገረቻቸውን ጉዳይ አምነው ውለው አደሩ፡ ምግብ ጠፋ፡ በነዚህ ሁለት ጎረቤቶች መካከል የሚፈጠረውን ለማየት ውሮም በቦታዋ አድፍጣ ቆየች፡፡
ቀናት አለፉ መሸም… ነጋም… የአሞራይቱና የአሳማዋ ልጆች በረሃብ አንጀታቸው ታጥፎ ሞቱ… የሞት ነገር ግን በዚህ አላበቃም አንዱ አንዱን አድፍጦ ሲጠብቅ ድመትም መጨረሻውን ለማየት ስትል ከቦታቸው ሳይነቃነቁ ሰነበቱ ረሀቡን ግን የቻለ ማንም የለም፡፡ ሁሉም በያለበት ፍንግል ፍንግል እያለ የሞትን ፅዋ ተጎነጩ፡ ሌሎችን አጣልታ ለመኖር ያቀደችው ውሮም በረሃቡ ምክንያት ህይወቷን ገበረች፡፡
ጌታ ሆይ የፍቅርን መንፈስ በላያችን አሳድር፡፡